Language
ታሪካችን

ስፕሪንግስ ኦፍ ሊቪንግ ዎተር

እ.ኤ.አ. በ 2019 የተመሰረተ ፣ ወጣት ሴቶችንና ህጻናትን ከኢትዮጵያ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ይታደጋል።

user_image

በረከት ማሞ

መስራች, ዋና ሥራ አስፈፃሚ

ኤስ ኤል ደብልዩ እንዴት ተመሰረተ?

የስፕሪንግስ ኦፍ ሊቪንግ ዎተር የሳምራዊው ቤት በመላው ኢትዮጵያ ከሚገኙ ሁለት የህገወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባዎች መጠለያዎች አንዱ ነው። ተጎጂዎች በሳምራዊው ቤት በሚቆዩበት ጊዜ ከአሰቃቂ ሁኔታ ነፃ የሆነ ድጋፍ እና አገልግሎት፣ መጽሐፍ ቅዱስ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች፣ እና የሙያ እና የህይወት ክህሎት ስልጠናዎችን ያገኛሉ። በዚህ ባለፈው ዓመት፣ የሳምራዊው ቤት 40 እንደዚህ ያሉትን ሰዎች አገልግሏል።

የወሲብ ንግድ ዝውውር ከህገወጥ የሰዎች ዝውውር ዓይነቶች አንዱ ወይም የዘመናችን ባርነት ሲሆን ግለሰቦች ለንግድ ወሲብ ዓላማ በማታለልና በማስገደድ የሚጓጓዙበት ተግባር ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር በአስከፊ ድህነት ውስጥ የሚኖሩ እና በኢኮኖሚ እና በፖለቲካ የተገለሉ ግለሰቦች ላይ ያነጣጠረ ነው። በርካታ ልብ የሚሰብሩ አስፈሪ ታሪኮችም አሉ።

በበረከት ማሞ የተመሰረተው የስፕሪንድስ ኦፍ ሊቪንግ ዎተር ዘፍጥረት ታሪክ አስደሳች እና አነቃቂ ነው። በረከት ማሞ ከአንድ አመት የዘርፉ ቆይታ በኋላ በፆታዊ ንግድ ምዝበራ ላይ ያሉ ሴቶች እና ልጃገረዶችን ችግር በመገነዘብ ከእነርሱ ጋር አዘውትራ መገናኘት ጀመረች። እናም 'ኢየሱስ ክርስቶስ ሕያው ውሃ ነው።' ብላ በማመን ለትርፍ ያልተቋቋመ ስፕሪንግስ ኦፍ ሊቪንግ ዎተር የተባለ የክርስቲያን ድርጅት መሰረተች።

የወሲብ ንግድ ዝውውርን አጠቃላይ በሆነ መንገድ መፍታት አካላዊ ፍላጎቶችን ማሟላት እንዲሁም የሕይወትን ውኃ ምንጭ የሚራቡና የሚጠሙ ሰዎችን መንፈሳዊ ፍላጎት ማሟላትን ይጨምራል። ኤስ ኤል ደብልዩ ወጣት ሴቶችንና ሕጻናትን ከህገወጥ የወሲብ ንግድ ይታደጋቸዋል። እናም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያገናኛቸዋል፤ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን እንደወደደው ይወዳቸዋል፣ መንፈሳዊ እና ቅድመ ሁኔታ የሌለው ፍቅር እና የሙያ ስልጠና ይሰጣል።

በዚህ ተልእኮ ከእኛ ጋር እንዲተባበሩ እንጋብዝዎታለን።

ስለ ኤስ ኤል ደብልዩ ለበለጠ ለመረዳት፣ እባክዎን በመስራቻችን የተዘጋጀውን ይህንን ቪዲዮ ይመልከቱ።

“የሕይወት ውኃ ወንዝ“ የሚለው ስም ከዮሐንስ ወንጌል የተገኘ ነው።

“እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ አላት።“

የዮሐንስ ወንጌል 4:14 TPT

'በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል...'

የዮሐንስ ወንጌል 7:38 AMPC

Springs of Living Water | All rights reserved | Copyright © 2023